አሁን ካናዳ ብለን የምንጠራው ወደዚች ምድር አዲስ የመጡ እንደመሆናችን መጠን እርምጃ መውሰድ እና የእውነት እና የእርቅ ሂደት አካል የሆነውን ሙሉ "እውነት" መማር አስፈላጊ ነው።
የካናዳ ተወላጆችን፣ ከቅኝ ግዛት በፊት እና በኋላ ታሪካቸውን፣ የበለፀጉ እና የተለያየ ባህላቸውን ፣ የአገሬው ተወላጆች ስምምነቶችን ፣ ፈርስት ኔሽን፣ ሜቲስ እና ኢኑይት የመሬት ይገባኛል ጥያቄዎችን እና የመኖሪያ ት/ቤት ስርዓትን የበለጠ ለመረዳት እንዲረዳዎት ከነዚህ ነፃ ኮርሶች ውስጥ አንዱን ይቀላቀሉ።